ንቅናቄው በልዩ ትኩረት እንዲፈጸም በፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ደረጃ ጠንካራ አቅጣጫ ተቀምጦ በሁሉም የምዝገባ ማዕከላት በአመራር የቅርብ ክትትል ድጋፍ እየተሰጠ እንደሚገኝ ታውቋል።፡
የዲጂታል መታወቂያ ካርድ (ፋይዳ) መመዝገብ የስልጣኔ ምልክት በመሆኑ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎችና የሕብረተሰብ ክፍል በሙሉ በየመመዝገቢያ ማዕከል ድረስ በመሄድ እንዲመዘገቡ ጥሪ ተላልፏል።
ጫሞ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ጨምሮ የትነበርሽ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ገሮ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በጫሞ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ምዝገባ እያካሄዱ ይገኛሉ።
አባያ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ሲቀላ 1ኛ ደረጃ እና በሬ ዕድገት በር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በዓባያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምዝገባ ያካሂዳሉ።
አርባምንጭ መሰናዶ ትምህርት ቤትና ኩልፎ 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በአርባምንጭ መሰናዶ ት/ቤት ላይ ምዝገባ ያካሂዳሉ
ልማት 2ኛ ደረጃ ት/ቤትና 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በልማት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ምዝገባ ያካሂዳሉ።
በተመሳሳይ ለነዋሪዎች በሼታ ክላስተር ላይ ቤሬ ቀጠና ምዝገባው ቀጥሏል።
ሲቀላ ክላስተር ላይ ጉርባ ቀበሌ ምዝገባው እየተካሄደ ይገኛል።
ልማት ክላስተር ላይ ሦስቱ የልማት ቀበሌ ቀጠናዎች ምዝገባ እያካሄዱ ሲሆን ህብረተሰቡ በጊዜ በመመዝገብ መታወቂያውን መወሰድ እንደሚገባም ተጠይቋል።